top of page

በዛብህ ወርቁ እና
ሰብለወንጌል ስምኦን

Bezabih Worku &
Seblewongel Simeon

የዔደን ኪዳን የጋብቻና የቤተሰብ አገልግሎት 

እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረው በኋላ የሰጠው ሃላፊነት በምድር እንዲበዛና በምድር ያለውን ሁሉ እንዲገዛ አንዲያስተዳድርና አንዲሰለጥን ነው። ይህንን ደግሞ ለማድረግ የተፈጠረው አዳም ብቻውን እንዳይሆን ረዳት ትሆነው ዘንድ ሄዋንን ከጎኑ አጥንት ወስዶ ወደ አዳም አምጥቶ የመጀመሪያው የወንድና የሴት መጣመር በኤደን ገነት ውስጥ በእግዚአብሔር አባትነት የጋብቻው ስርዐት ተከናውኗል። ይህም ለሰው ዘር ሁሉ የተሰጠ የብዜትና የገዢነት ጥምረት አንዲሆን ተደርጎ ባምላካችን በእግዚአብሔር ተሰራ። ዘፍ 2:21-24። ይህ በእግዚአብሔር የተሰራው የጋብቻ ስርዓትና ሕይወት አሁንም ባለነው ላይ እየሰራ ቢሆንም የጠላት ተግዳሮት የማያጣው ኅብረት ነው፤ ይህንን ደግሞ መከላከልና መጠበቅ የእያንዳንዱ ክርስቲያን ሃላፊነት ስለሆነ ሁላችንም ልንነቃና ወደዚህ ሰይጣን ወዳዘጋጀው ወጥመድ ውስጥ እንዳንገባ ጥንቃቄ በማድረግ የእግዚአብሔር ሃሳብ ፣ የመንግስቱ ስራ አንዳይበላሽ ተግተን ልንጠብቀው ይገባል። ለዚህም ከቤተክርስቲያን ጎን በመሰለፍ ይህ የከበረ የጋብቻ ኅብረት አንዲጠበቅ ለማድረግ ፣ ባለትዳሮችን፣ልጆችን፣ ወጣቶችን ባጠቃላይ ቤተሰብን ማዕከል ያደረገ አገልግሎት ለመስጠት ይህ የኤደን ኪዳን አገልግሎት ተመስርቶ በ IRS የታክስ ህግና ደንብ መሠረት በ (501 C3  ) ተመዝግቦ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል።

  • የአገልግሎቱ ራዕይ፤

      (Vision)

  • የእግዚአብሔር መንግስት ዓላማ በባለትዳሮች፣በልጆች፣በቤተሰብ ውስጥና በመበለቶች ተፈጻሚ ሆኖ ማየት።

  • የአገልግሎቱ ተልዕኮ መግለጫ፤

      (Mission Statement )

  • ጋብቻ በእግዚአብሔር የተሰራ ስለሆነ እንደ እግዚኣብሄር ቃል እየተመራ እንዲጠበቅና በምድር ላይ የእግዚአብሔር የመንግስት ስራ የሚታይበት ተቋም አንዲሆን ማድረግና የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሁሉ በዚህ የእውነት ቃል እንዲኖሩ ማነጽ።

  • የአገልግሎቱ ዕሴት፤

      (Our Value )

  • ለሰው ልጅ ሕይወት ዋናውና የመጨረሻው ባለስልጣን የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ

  • ጋብቻ ለእግዚአብሔር መንግስት ስራ መነሻ የመጀመሪያው ተቋም አንደሆነ፤

  • ጋብቻ በወንድና በሴት መካከል ብቻ የሚፈጸም አንደሆነ፤

  • የአገልግሎታችን መሠረት የእግዚአብሔር ቃል ብቻ አንደሆነ፤ 2ኛ ጢሞ 3:16-17, 1ኛ ቆሮ 2:1

  • ርህራሄ

  • በችግር ውስጥ የወደቁትን ቤተሰቦች ችግራቸውን በማድምጥ፣በመረዳትና የራስ በማድረግ ያለምንም ፍርድ ተስፋ እንዳለ በማበረታታት ማጠንከር

  • ታማኝነት

  • ሃላፊነትንና ተጠያቂነትን ዋና በማድረግ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመስርተን በምንናገረው ብቻ ሳይሆን በተግባር በመተርጎም ታማኝ ሆኖ መገኘት

  • ሁሉን አቀፍነት

  • በሰዎች መካከል ያለውን የዘርና የባህል ልዩነት በማክበር ሰውን በማንነቱ መቀበል

  • ተባባሪነት

  • በቤተሰብና በመበለቶች ዙሪያ ከሚያገለግሉ ክርስቲያናዊ ድርጅቶችን አብያተክርስቲያንት ጋር በመተባበር ለእግዚአብሔር መንግስት ስራ አብሮ መቆም

  • የአገልግሎቱ አፈጻጸም፤

      (Strategy)

  • ትምህርቶችን፣ ሴሚናሮችንና ስልጠናዎችን በማዘጋጀት

  • የግልና የጋራ የማማከር አገልግሎት በመስጠት

  • ጋዜጦችን፣ በራሪ ጽሁፎችንና መጽሄቶችን በማሰራጨት

  • ማናቸውንም የሚዲያ አገልግሎት በመጠቀም መልዕክቶችን በማስተላለፍ

  • ከአብያተክርስቲያናት ጋር  በትብብር በመስራት

  • የማማከር አገልግሎት ስልጠና በመስጠት

  • ከተመሳሳይ የአገልግሎት ዘርፎች ጋር ትብብር በማድረግ

Our Vision

The wellbeing of marriage and family life

Our Mission

To build healthy marriage and strengthen family-life based on biblical truth.

Statement of Faith

 

  • We believe that God is the creator of the universe creating both of the seen (physically) and the unseen (spiritually) realms and that God the creator is also the giver of life.

  • We believe that the Holy Bible is God’s word personally spoken by God for mankind for the purpose of revealing who He is and it is without error in all issues to which it speaks.

  • We believe Jesus Christ is divine God who came from heaven to mankind as a man yet retaining the divinity of God and who while living a sinless life was rejected and betrayed by man to be crucified and die on the cross yet not to remain dead but to resurrect the third day in accordance with his everlasting divine life.

  • We believe that the death of Jesus on the cross provided complete atonement for all the sins of the world therefore cleansing those who choose to be cleansed from their sin to then receive the Holy Spirit becoming ”Born Again” and being born again becoming children of God. Children in the family of God and as children in a personal relationship with their Father who is God above all and as children also inheritors in the heavenly kingdom of Jesus the kingdom that is without end.

  • We believe that Jesus is the judge of all of mankind’s thoughts, intentions, and actions and that he is just and wise in his judgment. As judge, Jesus will judge the unjust to everlasting condemnation while to the righteous he will give of His life, His gifts, and His glory.

  • We believe Jesus physically rose from the dead, was seen by and interacted with many eye witnesses including the disciples and apostles and that Jesus has now ascended back into heaven where he originally came from Jesus is currently seated on majesty, power and authority alongside the Father and He is now accessible to us in bother prayer and fellowship.

ABOUT 

ADDRESS

16526 S. STAGECOACH ST

Olathe, KS 66062

Email: edenvowministries@gmail.com

Tel: 913.406.2120

thumbnail.jpeg
  • Facebook
  • Youtube

CONTACT US

Thank You

This website is owned and operated by Eden Vow Marriage and Family Ministry.

All rights reserved ©2023.

bottom of page